Posted on 2024-04-01 10:12:48
በትምህርት ቤቶቹ መካከል የልምድ ልውውጥ ተካሄደ ሀረር መጋቢት 20/2016(ሀክትቢ) በሀረሪ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ ተካሄደ ። በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ አስተባባሪነት በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ ተካሂዷል። የልምድ ልውውጡ በቢሮው የትምህርት ቤቶች ማሻሻል ዳሬክቶሬት የተመራ ሲሆን ሐይቴክ አካዳሚ እና የሀረር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እየተገበሩት የሚገኘውን የመማር ማስተማር ሂደት መልካም ተሞክሮ በልምድ ልውውጡ አቅርበዋል። ትምህርት ቤቶቹ ባቀረቡት ተሞክሮ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ የሚደርጉትን ክትትል እና ቁጥጥር ሥርአት ለትምህርት ቤቶቹ ቀርቧል። በተለይ የወላጆች በትምህርት አሰጣጥ ሂደቱ ያበረከቱት አስተዋፆ ፣ የወላጆችን ተሳትፎ ማሳደግ የተቻለበቸው አሰራሮች፣ የመምህራን የተቀናጀ አሰራር ፣የተማሪዎች የስነልቦና ብሎም ለፈተና የሚረጉ ዝግጅቶች እና በቲቶሪያል ፕሮግራሞች የተገኙ ውጤቶች እንደ መልካም ተሞክሮ ቀርበው ዉውይይት ተካሂዶባቸዋል። ትምህርት ቤቶቹ በተከተሏቸው የመማር ማስተማር ሂደቶች አመርቂ ውጤቶች ማስመዝገባቸውን ገልፀዋል። በልምድ ልውውጡ የተሳተፉ ትምህርት ቤቶች በበኩላቸው በተለይ ተማሪዎችን ለ12ኛ ክፍል ፈተና ለማዘጋጀት የሚያስችሉ የመማር ማስተማር ሂደቶች ላይ ጥሩ የሚባል ልምድ ያገገኙበት መሆኑን ገልፀዋል። በልምድ ልውውጡ ላይ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሱፐርቫይዘሮች፣ዋና እና ምክትል ርእሳነ መምህራን እንዲሁም የትምህርት ቤት ማሻሻል ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
Total visitors: 1130