Posted on 2024-04-21 20:52:27
Organizational culture (ተቋማዊ ባህል ) በሚል ሰነድ ዙሪያ ለዳይሬክቶሬቱ ፈፃሚዎች ግንዛቤ ፈጠረ !! ሀረር ፤ ሚያዢያ 11/2016(ሀክትቢ) የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳይሬክቶሬት ተቋማዊ ባህል በሚል ሰነድ ዙሪያ ለዳይሬክቶሬቱ ፈፃሚዎች፣ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮች እና ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ፈጠረ። ዳይሬክቶሬት በየሳምንቱ በሚያካሄደው የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ላይ በዛሬው ዕለት ተቋማዊ ባህል በሚል ሰነድ ዙሪያ ለዳይሬክቶሬቱ ፈፃሚዎች፣ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ውይይት ተካሂዷል ፡፡ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙክታር ሁሴን በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የዕውቀት ሽግግር መድረኩ በርካታ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ፣ለበለጠ ስራ የሚያነሳሱ የህይወት ተሞክሮዎች የሚገኝበት የጎለበተ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
Total visitors: 1122