Home







Recent News


Recent News

Gallery





በሐረር ከተማ በጎዳና ተዳዳሪነትና ልመና ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ችግር ለመፍታት ተቋማዊ አሰራርን በማጎልበት ችግሩን የመቅረፍ ስራ በትኩረት ይሰራል:- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

Posted on 2024-04-17 06:31:21


በሐረር ከተማ በጎዳና ተዳዳሪነትና ልመና ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ችግር ለመፍታት ተቋማዊ አሰራርን በማጎልበት ችግሩን የመቅረፍ ስራ በትኩረት ይሰራል:- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

በሐረር ከተማ በጎዳና ተዳዳሪነትና ልመና ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ችግር ለመፍታት ተቋማዊ አሰራርን በማጎልበት ችግሩን የመቅረፍ ስራ በትኩረት ይሰራል:- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በዋናነት በከተማው በጎዳና ተዳዳሪነትና ልመና ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ፣የጉዳት ተጋላጭነታቸውን ለመከላከልና ቁጥጥር ለማድረግ የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት በማድረግ አጽድቋል። የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ እንደተናገሩት ሐረር ለነዋሪዎቿ ምቹ ለጎብኚው ሳቢና ማራኪ የማድረግ ስራ መጎልበት አለበት ብለዋል። በተለይ በከተማዋ ውስጥ የሚታየው የጎዳና ተዳዳሪነትና ልመና መበራከት ፈተና እየሆነ መምጣቱን አመልክተዋል። የክልሉ መንግስት በከተማው ውስጥ የሚገኙትን ጎዳና ተዳዳሪዎችን በመደገፍ ቁጥሩ እንዲቀንስ ስራዎች ቢከናወኑም ውጤት ማምጣት አለመቻሉን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅተም በከተማው የሚታየው የጎዳና ተዳዳሪ እና በጎዳና ላይ የሚከናወኑ ልመና መበራከት የማህበራዊ ቀውስ ችግሮችን ስለሚያስከትል በጋራ መከላከል መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። በተለይ ችግሩን በዘለቄታነት ለመፍታት ተቋማዊ አሰራር ማጎልበትና የህግ ማእቀፍ አሰራርን ተግባራዊ የማድረግ ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። በተጨማሪም ወጣቶች ወደ ጎዳና ተዳዳሪነት እንዳይወጡ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋትና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራዊ የሆነ ስራዎችን በማከናወን ችግሩን ከምንጩ መቅረፍ እንደሚገባም አመላክተዋል። መስተዳድር ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ከዛሬ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ ሰራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ውሳኔ አስተላልፋል።

Total visitors: 1125

List of Comments (0)




Leave a Comment:

Name:
Email:
comment:

ADDRESS

Harari Region,
P.O. Box 138,
Phone:+251-09-1514-0787,
derejealmayhu7@gmail.com

Follow us on

Online: 10052

Visitors: 10052
Users: 0

Copyright@2022 HPRSEB All rights reserved.                                                                Developed By:DEREJE ALMAYHU