Posted on 2024-04-06 18:35:03
በሀገራዊ ለውጡ የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላችንን እንወጣለን:- የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ መስኮች የተገኙ ውጤቶች በቀጣይም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተመዘገቡ ስኬቶችን በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በሀረሪ ክልል ተካሂዷል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ሰላማችን በእጃችን!፣ በጋራ ጥረት ሰላማችንን አረጋግጠን ለሀገራችን ብልጽግና እውን መሆን እንተጋለን! ፣ አንድነታችንን በማጽናት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናፋጥናለን!፣ ከብልጽግና ጋር የማንፈታው ችግር የለም! የሚሉና መሰል መልዕክቶች አስተላልፈዋል። የሰልፉ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መሪነት የለውጡ መንግስት ተጨባጭ ለውጥና እድገት እያስመዘገበ ነው ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መሪነት ሀገርን ከድህነት ለማውጣት በተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተሰፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ መስኮች በተከናወኑ የልማት ሥራዎች ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፣ በቀጣይም ይሄ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። በሀረሪ ክልልም ከለውጡ በኋላ የህዝብን አንድነት የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ባለፉት ስድስት የለውጥ ዓመታት በልማትና በመልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ በክልሉ መሠረታዊ ለውጦች መመዝገብን ገልጸዋል። የለውጡ መንግስት በክልሉ የግብርና ልማትና የቱሪዝም ሃብት ጎልቶ እንዲወጣ ማድረጉንም አስረድተዋል። ባለፉት ዓመታት በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በሌሎች የልማት ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች በቀጣይም እንዲጠናከሩ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ነው የገለጹት። በለውጡ መንግስት ለተመዘገቡ ድሎች አስፈላጊውን ድጋፍና እውቅና በመስጠት ለተጨማሪ ውጤት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።
Total visitors: 1131