Posted on 2024-04-17 06:28:48
በአመራር መብሰል በሚል ሰነድ ዙሪያ ለዳይሬክቶሬቱ ፈፃሚዎች ግንዛቤ ፈጠረ !! ሀረር ፤ ሚያዢያ 4/2016(ሀክትቢ) የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳይሬክቶሬት በአመራር መብሰል በሚል ሰነድ ዙሪያ ለዳይሬክቶሬቱ ፈፃሚዎች፣ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮች እና ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ፈጠረ። ዳይሬክቶሬት በየሳምንቱ በሚያካሄደው የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ላይ በዛሬው ዕለት በአመራር መብሰል በሚል ሰነድ ዙሪያ ለዳይሬክቶሬቱ ፈፃሚዎች፣ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ውይይት ተካሂዷል ፡፡ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙክታር ሁሴን በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የዕውቀት ሽግግር መድረኩ በርካታ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ፣ለበለጠ ስራ የሚያነሳሱ የህይወት ተሞክሮዎች የሚገኝበት የጎለበተ መድረክ በመሆን እያገለገለ መሆኑን በመጥቀስ በዛሬው መድረክ የተገኛችሁ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮችም በየትምህርት ቤታችሁ ይሄንን መሰል መድረክ በመፍጠር በትምህርት አመራሩና በመምህራኑ መካከል የሚታየውን የዕውቀትና የክህሎት ልዩነት ለማጥበብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስለሚያበረክት ይሄንን ተሞክሮ ማስፋት እንደሚጠብቅባቸው ገልፀዋል ፡፡
Total visitors: 1133